የአዲስ አበባ የላዳ ታክሲ ማህበራት ከ387 ሺህ ብር በላይ ቦንድ ገዙ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ የላዳ ታክሲ ማህበራት ከ387 ሺህ ብር በላይ ቦንድ ገዙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13/2013(ኢዜአ) በአዲስአበባ የሚገኙ የላዳ ታክሲ ማህበራት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ387 ሺህ ብር በላይ የቦንድ ግዢ አካሄዱ፡፡
ግዢውን ያካሄዱት ማህበራት ከ10ሺህ በላይ አባላት ናቸው፡፡
የማህበራቱ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም መለሰ ቦንዱን ለአዲስ አበባ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስረክበዋል፡፡
ማህበራቱ ቦንዱ የገዙት ማህበራዊና አገራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም ድጋፍ ከማድረግ እንደማይቆጠቡ ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ለግድቡ ግንባታ የሚደረግ ድጋፍ ራስን መደገፍ ማለት ነው፡፡
ማህበራቱ ላደረጉት ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ማህበራቱ አስተዳደሩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ከ575ሺህ ብር በላይ እንደለገሱም ተገልጿል፡፡