ህብረተሰቡ 14 የሚሆኑ የለውዝ ቅቤ ምርቶችን እንዳይጠቀም ባለስልጣኑ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13/2013(ኢዜአ) ህብረተሰቡ ከፍተኛ የሆነ የአፍላ ቶክሲን /Aflatoxine/ የተገኘባቸውን 14 የለውዝ ቅቤ ምርቶችን እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ባደረገው ቁጥጥርና ፍተሻ አማካኝነት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ምርቶቹ ከፍተኛ አፍላ ቶክሲን /Aflatoxine/ እንደተገኘባቸው ገልጿል፡፡

ለውዞቹን የሚያመርቱ ተቋማትም ላይ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ አምራቾቹን ለማግኘት አለመቻሉንም  አስታውቋል፡፡

የሚመለከተቻው የቁጥጥር አካላት ምርቶች ከገበያ ላይ በመሰብሰብ እንዲያስወግዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

ባለስልጣኑ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ያገዳቸው የለውዝ ቅቤዎች የሚከተሉት ናቸው

1ኛ ምስራቅ የለውዝ ቅቤ

2ኛ ሳራ የለውዝ ቅቤ

3ኛ ዳና የለውዝ ቅቤ

4ኛ ሰገን የኦቾሎኒ ቅቤ

5ኛ አርሂቡ የለውዝ ቅቤ

6ኛ ረጃት የለውዝ ቅቤ

7ኛ ኢትዮ የለውዝ ቂቤ

8ኛ ጽዮን የለውዝ ቅቤ

9ኛ ማሀሩን የኦቾሎኒ ቅቤ 

10ኛ ላቪሊ የሎዝ ቂቤ 

11ኛ እናት የሎዝ ቅቤ 

12ኛ ኤ.ኤፍ የሎዝ ቅቤ 

13ኛ መና የኦቾሎኒ ቅቤ

14ኛ ሂር የለውዝ ቅቤ

መሆናቸውን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም