ጅማ አባጅፋር የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫውን አነሳ

102
ሐምሌ 9/2010 ጂማ አባጅፋር ዛሬ አዳማ ከነማን 5-0 በማሸነፍ ፕሪሚየር ሊጉን በተቀላቀለበት የመጀመሪያ ዓመት ዋንጫውን አንስቷል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2010 ውድድር ዛሬ ተጠናቅቋል፡፡ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር እኩል የዋንጫ እድል  ይዞ  ሀዋሳ ከነማን የገጠመው ቅድስ ጊዮርጊስ 2-0  ማሸነፍ ቢችልም በግብ ተበልጦ ዋንጫውን አጥቷል፡፡  ቅድስ ጊዮርጊስና ጅማ አባ ጅፋር እስከ መጨረሻው ሳምንት እኩል ነጥብና እኩል የግብ  ክፍያ ይዘው መቆየታቸው ይታወሳል፡፡  ወልዲያ ከነማ፣ አርባ ምንጭ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ  ከፕሪሚየር ሊጉ ተሰናብተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ፕሪሚየር ሊጉን በሶስተኝነት አጠናቅቋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም