ፌስቡክ 100 ተጨማሪ ቋንቋዎችን የሚተረጉም መተግበሪያ ይፋ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ፌስቡክ 100 ተጨማሪ ቋንቋዎችን የሚተረጉም መተግበሪያ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ጥቅምት 10/2013 (ኢዜአ) ፌስቡክ 100 ተጨማሪ ቋንቋዎችን የሚተረጉም አዲስ መተግበሪያ ይፋ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ይህ አርቴፊሼል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌር የተሰራው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ከ2 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎችን በ160 ቋንቋዎች የ ማህበራዊ ትስስራቸውን ለማጠናከር እንደሆነ ሲጂቲኤን አስነብቧል፡፡
አዲሱ የትርጉም ውጤት ለፌስቡክ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ያሉት የምርምሩ ረዳት አንግላ ፋን አዲሱ መተግበሪያ ለግዙፉ ፌስቡክ ድርጅት የዓመቱ ምርጥ ስራ ሲሉም አሞካሽተውታል፡፡
ከዚህም በላይ አዲሱ ሞዴል በእንግሊዝኛ ቋንቋ ላይ መሰረት አለማድረጉ ትክክለኛነቱን አስተማማኝ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
በበፊቱ የፌስቡክ የትርጉም አሰራር ቻይንኛን ወደ ፈረንሳይኛ ለመለወጥ በቅድሚያ ቻይንኛን ወደ እንግሊዘኛ መለወጥ ግዴታ የነበረ ሲሆን የአዲሱ መተግበሪያ ግን ቻይንኛን በቀጥታ ወደ ፈረንሳይኛ መተርጎም ያስችላል እንደ ነው የተባለው፡፡
በየቀኑ ከ20 ቢሊዮን በላይ ትረጉሞችን አስተናግዳለው የሚለው ፌስቡክ አደሱ አሰራር ይህን እና ሌሎች ስራዎችን እነደሚያቀላጥፍለት እምነት አንዳለው በመረጃው ተካቷል፡፡
የማሽን ትርጉም የተለያዩ ቋንቋን በሚናገሩ ሰዎች መሃል ያለን ልዩነት ለመቅረፍ እና እንደ ኮቪድ ላሉት አንገብጋቢ ጉዳዮች ትክክለኛ መረጃን ለህዝብ ለማድረስ ያለው ጥቅም ትልቅ ነው ሲል ሲጂቲኤን አስነብቧል ፡፡