ጀርመን የኮቪድ 19 በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ የአየር ማቀዝቀዣ ስርዓትን ለማሻሻል 500 ሚሊዬን ዩሮ ስራ ላይ ልታውል ነው - ኢዜአ አማርኛ
ጀርመን የኮቪድ 19 በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ የአየር ማቀዝቀዣ ስርዓትን ለማሻሻል 500 ሚሊዬን ዩሮ ስራ ላይ ልታውል ነው
አዲስ አበባ ጥቅምት 9/2013 (ኢዜአ) ጀርመን የኮቪድ 19 በሽታ ስርጭትን ለመከላከል ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ህንጻዎች ላይ 500 ሚሊዬን ዩሮ በመመደብ የአየር ማቀዝቀዣ የማሻሻል ስራ ልታከናውን ነው።
እንደ ቢ ቢ ሲ ዘገባ ገንዘቡ የሚውለው በመንግስት የአገልግሎት መስጫ ቢሮዎች፣ በሙዚየሞች ፣በቲያትር ቤቶች፣ በዩንቨርስቲዎችና በትምህርት ቤቶች የአየር ዝውውሩን ለማሻሻል ነው።
ቫይረሶች አየር ላይ ቢያንስ ለስምንት ደቂቃዎች ሊቆዩ እንደሚችሉ ጥናቶች ማመላከታቸውም ተመልክቷል።
የአየር ማቀዝቀዣ ሲስተሞችን ለማሻሻል ስራው የተመደበው በጀት ከማክሰኞ ጀምሮ ማሰራጨት እንደሚጀመር ተጠቅሷል።
በመንግስት በኩልም ማዕከል ላይ ያለ የአየር ማቀዝቀዣ ሲስተም የሌላቸው ትምህርት ቤቶች ቢያንስ ተንቀሳቃሽ አየር የሚያጣሩ መሳሪያዎችን እንዲያስገቡ እንደሚፈለግ በዘገባው ተጠቁሟል።