ቀጥታ፡

የተለያዩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከዘንድሮው የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት በላይ ዕዳ አለባቸው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9(2013)በኢትዮጵያ የየመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከዘንድሮው የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት በላይ ዕዳ ያለባቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ ልዩ ስብሰባ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በማብራሪያቸውም የስኳር ፋብሪካዎች፣ ኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)ና ሌሎች የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ጨምሮ ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ አለባቸው ብለዋል።

የኩባንያዎቹ ዕዳ ከዘንድሮው የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት በላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

በመሆኑም የድርጅቶቹ ዕዳ ከፍተኛ በመሆኑና መክፈልም ስለማይችሉ መንግሥት ማሻሻያ በማድረግ ከእዳ ነጻ አድርጓቸዋል ብለዋል።

መንግሥት ይህንን ማሻሻያ አድርጎ መፍትሄ ባያስቀምጥ ኖሮ፤ እያንዳንዱ ኩባንያ በዕዳ ተውጦ ይቀሩ ነበር ብለዋል።

የፌዴራል መንግሥት ለ2013 በጀት ዓመት ከ476 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ማጽደቋ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም