የጣና ሃይቅን እምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ ዛሬ ተጀምሯል

ባህርዳር  ጥቅምት 9/2013 (ኢዜአ) በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም የማስወገድ ስራ ዛሬ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ምጽርሃ ቀበሌ ተጀምሯል ።

በማስጀመር ስነ-ስርዓቱ ላይ የፌዴራል ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ፣ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገርና የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ ተገኝተዋል።

ዛሬ በተጀመረው በዚህ ዘመቻ ላይ ሌሎችም የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም የዘመቻው ተሳታፊዎችም በስፍራው ተገኝተዋል።

ከጥቅምት 9/2013 እስከ ሕዳር 9/2013 በሚዘልቀው ዘመቻ ላይ ከ360 ሺህ በላይ ሰው እንደሚሳተፍ የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ቀደም ሲል ማስታወቁ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም