የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው

61

ጥቅምት 9/2013 (ኢዜአ) 5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው።

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተገኝተዋል።

ምክር ቤቱ 6ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር መነሻ በማድረግ ከምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለተነሱላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም