ቀጥታ፡

ከነገ ጀምሮ ከ100 ሺህ ብር በላይ እጃቸው ላይ የሚገኝ ግለሰቦች ገንዘብ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6/2013(ኢዜአ) ከነገ ጀምሮ ከ100 ሺህ በላይ ነባሩን ብር በእጃቸው በግለሰቦች እጅ የሚገኝ ነባሩ ብር ተወርሶ ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ተናገሩ።

ከነገ ጀምሮ ገንዘብ መቀየር የሚቻለው ከ100 ሺህ ብር በታች ብቻ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ዶክተር ይናገር ይህን የተናገሩት የገንዘብ ቅያሪውን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።  

ገዥው እንደገለጹት፤ ከ100 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በአዲሱ የገንዘብ ኖት ለመቀየር የተቀመጠው ቀነ ገደብ ዛሬ አብቅቷል።   

እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ለመቀየር የተያዘው የጊዜ ገደብ እንደማይራዘምም ጠቁመዋል።

ይህን ተከትሎ ከነገ ጀምሮ እጃቸው ላይ ከ100 ሺህ ብር በላይ የያዙ ግለሰቦች ገንዘባቸው ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ነው ያሉት ዶክተር ይናገር፡፡  

ከ100 ሺህ ብር በታች የቀድሞውን የገንዘብ ኖት ይዘው የሚመጡ ሰዎች ግን ከነገ ጀምሮ እንደሚስተናገዱ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ከ100 ሺህ ብር በታች የገንዘብ ቅያሪው ለሁለት ወራት እንደሚቀጥልና አፈጻጸሙ እየታየ የጊዜ ገደቡ ሊያጥር እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡

ባንኩ በቀሩት ጊዜያት በአርሶና አርብቶ አደሩ እጅ የሚገኘውን ገንዘብ የመቀየር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም