ቀጥታ፡

በዓለም ላይ ለሞት ከሚዳርጉ ህመሞች የልብነክ በሽታዎች የመጀመሪያውን ድርሻ ይስወዳሉ---የጤና ሚኒስቴር

ጥቅምት 7/ 2013 (ኢዜአ) በዓለም ላይ ሰዎችን ለሞት ከሚዳርጉ ህመሞች መካካል የልብነክ በሽታዎች የመጀመሪያውን ድርሻ እንደሚወስዱ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ ገለጹ።

“ደም ግፊትዎን ይለኩ፣ ደምግፊትዎን ይቆጣጠሩ እና ረጅም እድሜ ይኑሩ” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የከፍተኛ ደምግፊት ቀን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫውም በዓለም ላይ በየዓመቱ ከሚሞቱት ሰዎች ውስጥ 31% የሚሆኑት ሰዎች በልብነክ በሽታዎች ሳቢያ የሚሞቱ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ዶክተር ደረጀ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ኮሚሽን ሪፓርት እ.ኤ.አ በ2018 ባወጣው ሪፖርት በአገራችን በተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎችና በድንገተኛ አደጋ በየአመቱ ከሚሞቱት ሰዎች ውስጥ የልብነክ በሽታዎችና ካንሰር ተደምረው በአጠቃላይ 54 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ የሚወስድ ነው።

በአሁኑ ወቅትም የልብነክ በሽታዎች ዋነኛ የሞት መንስኤዎች ናቸው ብለዋል፡፡

ጤናማ ያልሆነ አመጋገብና የደምግፊት መጨመር ዋነኛ ለልብ ነክ በሽታዎች አጋላጭ መንስኤዎች መሆኑን አመልክተው በወቅቱ ህክምና መጀመርና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ በሽታውን ለመግታት ያግዛል ነው ያሉት፡፡

የልብ ጤናችንን ለመጠበቅ የደም ግፊት ምርመራ ማድረግ ባህል ማድረግ ይገባል ሲሉ ዶ/ር ደረጀ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የደም ግፊታችን ጤናማ ሆኖ እንዲቆይና የልብ ጤናችን የተጠበቀ እንዲሆን፤ በየቀኑ ለ30 ደቂቃ ፣ በሳምንት ቢያንስ ለ5 ቀናት አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ጨው መጠን፣ ቅባትና ስኳር የበዛባቸውን ምግቦች መመገብ በመቀነስ፣ ስጋራ አለማጨስና ከቺሱም ተጋላጭ ባለመሆን፣ ጎጂ የሆነ አልኮል መጠን ባለመውሰድና በጤና ባለሙያ የሚታዘዘውን መድሀኒት በአግባቡ በመውሰድ የልብነክ በሽታዎችን መከላከል እንደምቻል የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ አስገንዝባዋል።

አክለውም አትክልትና ፍራፍሬ አዘውትረው መመገብም ተገቢ መሆኑን በሚኒስቴሩ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ተመልክቷለል፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም