ቀጥታ፡

ሹራ የለንደን ማራቶንን ያሸነፈበት ምስጢር

አዲስ አበባ ጥቅምት 5/2013 (ኢዜአ) የለንደን ማራቶንን ያሸነፈው ሹራ ቂጣታ ውድድሩን ያሸነፈበትን ምስጢር ለእንግሊዝ ዜና ማሰራጫ (ቢቢሲ) አስታውቋል፡፡

ጣቢያው ኢትዮጵያዊው አትሌት የዓለምን የማራቶን ውድድር ከሁለት ሰዓት በታች የገባውን ኬንያዊው ኢሉዪድ ኪፕቼጌ  ያሸነፈበትን ''ምስጢር'' ይዞ ወጥቷል፡፡

''ኢሉዪድ ኪፕቼጌን ለማሸነፍ ምን ይጠይቃል?'' በሚል ርዕስ በወጣው ጽሁፍ ሹራ ውድድሩን ያሸነፈበትን ምክንያቶች ዘርዝሯል፡፡

''ከባድ ልምምድ፣ተሰጥኦና  ከውድድሩ በፊት የተመገበው ጥሩ ቁርስ፡፡''

ከአንድ ዓመት በፊት በዚሁ ከተማ የተካሄደውን ውድድር አራተኛ ሹራ ወጥቶ ነበር፡፡ኪፕቾጌ አንደኛ ሲወጣ፡፡

ታዲያ በያኔው ውድድር ሹራ ፍራፍሬ ብቻ ቁርስ በልቶ ወደ ሩጫው ይገባል፡፡35 ኪሎ ሜትር እንደሮጠ ረሃብ ጀርባውን ይፈትገው ገባ፡፡

ታዲያ ዘንድሮ ከዚያ ስህተቱ ተምሮ ቁርሱን እንክት አድርጎ መብላቱን ተናግሯል፡፡''ያልበላሁት ነገር የለም፡፡''

'ሾርባ፣ዳቦ፣እንቁላል፣እርጎና ኃይል ሊሰጠኝ የሚችል ሁሉ፡፡ያም ኃይል ሰጥቶን ጦርነቱን ለማሸነፍ ረዳኝ'' ብሏል፡፡

በውድድሩ ያሸንፋል ተብሎ የተጠበቀው ቀነኒሳ በቀለ በገጠመው ችግር የጤና እክል ሳይወዳደር መቅረቱ ይታወሳል፡፡

ሹራ ውድድሩን ያሸነፈው በሁለት ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በመግባት ነበር፡፡

   ውድድሩን ያሸንፋል ተብሎ የተጠበቀው ኪፕቾጌ ስምንተኛ ወጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም