ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ጎበኙ

ጥቅምት 3/2013 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ዛሬ ጎብኝተዋል።

ግድቡ በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 200 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል ሲሆን በዓመት ደግሞ 6 ሺህ ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።

የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም በአሁኑ ወቅት 36 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከኃይል ማመንጫነት ባሻገር ለቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆንም ይጠበቃል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

በግንባታ ላይ የሚገኘው የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአንድ ወር በፊት መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም