በቤንች ማጂ ዞን በደረሰ የድንጋይ ካባ ናዳ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ

68
ሚዛን ሀምሌ 8/2010 በቤንች ማጂ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ በደረሰ የድንጋይ ካብ ናዳ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዘርፍ አስተባባሪ ኢንስፔክተር ውብሸት ካሳ እንዳሉት አደጋው የደረሰው ትናንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ በወረዳው ኡጽቅን ቀበሌ ልዩ ስሙ ጋቸብ ድልድይ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ነው፡፡ በማህበር ተደራጅተው ድንጋይ ከሚያወጡ ሴቶች መካከል በድንጋይ ቁፋሮ ሥራ ላይ በነበሩ ሁለት ሴቶች ላይ የድንጋይ ካቡ ተደርምሶ አደጋው መድረሱን ገልጸዋል፡፡ በአደጋው የአንዷ ሴት ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ ሁለተኛዋ ተጎጂ በግል ጤና ተቋም የሕክምና እርዳታ እየተደረገላት ትገኛለች። ኢንስፔክተሩ እንዳሉት በድንጋይ ማውጣትና መሰል ተግባር ላይ የተሰማሩ ዜጎች ሁልጊዜ ሥራቸው ሲያከናውኑ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም