ቀጥታ፡

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 76 በመቶ በላይ ደርሷል--ሚኒስትር ስለሺ

አዲስ አበባ መስከረም 30/2013 (ኢዜአ) የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 76 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ አስታወቁ።

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ የሚኒስቴሩንና የተጠሪ ተቋማትን የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ የሥራ አፈፃፀም አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመጠጥ ውሃ፣ በመስኖ ልማት፣ በኢነርጂና በተፋሰስና የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር  ክንውኖች ተዳሰዋል።

በዚህም  የግድቡ ግንባታ  ከሩብ ዓመት በፊት ከነበረበት የሁለት በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ሚኒስትሩ  አስታውቀዋል።

ከሕዝቡ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገው ተሳትፎ በማጠናከሩም በሩብ ዓመቱ  ብቻ 272 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል።

በንጹህ ውሃና ሳኒቴሽን  ዘርፍ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በተከናወነው ሥራ ለ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተጠቃሚ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ከክረምት ጋር ተያይዞ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ መስተጓጎል መታየቱን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በሩብ  በአጠቃላይ የመስኖ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም በአማካይ ከ12 እስከ 40 በመቶ ማደጉን  አስታውቀዋል።

ለአገር ውስጥና ለውጭ ከተሸጠው ኢነርጂ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ  መገኘቱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ከዚህም ውስጥ ለሱዳንና ጅቡቲ ከተሸጠው ኃይል የተገሸው 28 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነም ተናግረዋል።

የአገሪቱን ውሃ ሀብት  ለማስጠበቅ  ከተፋሰስ አገሮች ጋር የሚደረገ ድርድርና ትብብር መቀጠሉም ኢንጂነር ስለሺ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም