ቀጥታ፡

የእንጦጦ ፓርክ የምርቃት ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

መስከረም 30 /2013 (ኢዜአ) ሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት አካል የሆነው የእንጦጦ ፓርክ የምርቃት ስነ ስርዓት በመካሄድ ላይ ነው።

ፓርኩ አገርኛ ስያሜዎችን እና መዝናኛ ዘርፎችን ባካተተ መንገድ የተገነባ ሲሆን፣ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩም ተገልጿል።

በዚህም በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለዘመናት እንጨት በመልቀም ኑሯቸውን ሲገፉ ለነበሩ 463 እናቶች የሚሰሩበት የቁልፍ እርክክብ አድርገውላቸዋል።

በፓርኩ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን የመስቀል ስነ-ስርዓት ከተከናወነ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፓርኩ ላይ በተዘጋጀው ቦታ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።ፓርኩ ከተመረቀ በኋላ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም