የጉለሌ ክፍለ ከተማ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገለጸ

አዲስ አበባ መስከረም 27/2013 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገለጸ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ በአስሩም ወረዳዎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮችን አከናውኗል።
በዚህም ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በላይ ደጀን ገልጸዋል።
በቀጣይም ግድቡን በተመለከተ በሚሰራው ስራ ላይ ከዚህ በበለጠ ለመስራት እንደሚተጉ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ምስክር ነጋሽ በበኩላቸው" የህዳሴ ግድቡ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን የማንነታችንና የነጻነታችን መገለጫ ጭምር ነው ብለዋል።"
የህዳሴ ፕሮጀክት ድል ተጎናጽፈን ድህነትን ሰብረን የምንወጣበት በመሆኑ ንቅናቄውን በማስቀጠል ዳር ማድረስ ይገባናል ብለዋል።
በቀጣይ ለሚከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የህዳሴውን ዋንጫ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ተረክቧል።