አርባ ምንጭ ከነማ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱ ተረጋገጠ - ኢዜአ አማርኛ
አርባ ምንጭ ከነማ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱ ተረጋገጠ

አርባምንጭ ሰኔ 7/2010 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ አርባ ምንጭ ከነማ ዛሬ ፋሲል ከነማን አስተናግዶ አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም ከመውረድ ሳይድን ቀረ ፡፡ በወራጅ ቀጠና ውስጥ የነበሩ ኢትዮ ኤሌክትሪክና ወላይታ ዲቻ ድል በመቀዳጀታቸው በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየት ተስፋቸዉን ሲያረጋግጡ አርባ ምንጭ ከነማ የእነሱን መሸነፍ ቢጠባበቅም ሳይሳካለት ቀርቷል ፡፡ በ2003 ዓ.ም. ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለው አርባ ምንጭ ከነማ /አዞዎቹ / ከሰባት ዓመታት በኋላ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ አርባምንጭ አንድ ለባዶ ያሸነፈበት የዛሬው ጨዋታ ከበቃ በኋላ የፋሲል ከነማ አሠልጣኝ መሳይ ተፈሪ በሰጡት አስተያየት አርባ ምንጭ ከነማ የተሻለ ተጫውቶ ማሸነፉ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአርባ ምንጭ ከነማ ምክትል አሠልጣኝ ማቴዎስ ለማ ግን አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል ፡፡