ቀጥታ፡

በመዲናዋ ለተማሪዎች የሚሆን 5 ሚሊየን ማስክና ለትምህርት ቤቶች 3ሺህ የውሃ ማጠራቀሚያ ሮቶዎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26/2013 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ ለተማሪዎች የሚሆን 5 ሚሊየን የአፍ እና የፊት መሸፈኛ ጭብሎች እና ለትምህርት ቤቶች 3ሺህ የውሃ ማጠራቀሚያ ሮቶዎች ድጋፍ ተደረገ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለተማሪዎች ምገባ ፣ የትምህርት ቁሳቁስ ፣ቦርሳ እና ጫማ እንዲሁም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዳይጋለጡ ማስክ ለማቅረብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብሮችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭ በማያደርግ መንገድ ትምህርት ለማስጀመር ለሚደረገው ዝግጅት የተለያዩ ድርጅቶች በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ጉያ ቴክስታይል ጋርመነት ደረጀውን የጠበቀ 5 ሚሊየን የአፍ እና የፊት መሸፈኛ ሜዲካል ማስኮችን ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡

የግል እና የመንግስት ተቋማትን አንድ ላይ የያዘ ጥምረት ለሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚሆን 3 ሺህ የውሃ ማጠራቀሚያ ሮቶዎችን ድጋፍ ጤናችን በእጃችን safe hands " በዳልበርግ ግሩፕ እና በሮሃ ግሩፕ የተባለ ድርጅት ድጋፍ ባድረጉን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ ማዕድን አልሚዎችን በማስተባበር አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ በሚል የ300 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ 2050 ተግዳሮቶች እና ድሎች ማህበር መንግስት ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሚያደርገው ርብርብ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት 35ሺህ ማስኮችን ማበርከቱን የአዲስ አበበባ ፕሬስ ሰክሪያት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ አመልክቷል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ርክክቡ ወቅት እንደገለጹት ዛሬ የተደረጉት ድጋፎች ተማሪዎች ለኮቪድ-19 ወረርሽን ተጋላጭ እንዳይሆኑ እጅግ አስፈላጊ ቁሳቁሶች በመሆናቸው ድርጅቶቹ ላደረጉት ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ እና በተማሪዎች ስም ምስጋና ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም