ቀጥታ፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የካሜሩን አምባሳደርን የሹመት ደብዳቤ ቅጅ ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26/2013(ኢዜአ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኢትዮጵያ የካሜሩን አምባሳደርን የሹመት ደብዳቤ ቅጅ ዛሬ ተቀበሉ።

አምባሳደር ሬድዋን በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የሁለቱ አገሮች ግንኙነትን ለማጠናከር በቁርጠኝነት ትሰራለች።

አገሮቹ ከሁለትዮሽ ግንኙነት በተጨማሪ በክልላዊና ዓለም አቀፋዊ መድረኮች ትብብራቸውን ማጎልበት  እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካሜሩን በየቀኑ የሚያደርገው በረራ በአገሮቹ  የሚኖረውን የገበያ ትስስር ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥርም ሚኒስትር ዴኤታው አንስተዋል።

አምባሳደር ኢዊምቢዩ ሞኖኖ በበኩላቸው በኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን በመሾማቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ አገሮቹ  ያሏቸውን የጋራ እሴቶች ለማጠናከር  እንደሚሰሩ አመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኖቤል ሰላሚ ተሸላሚ መሆናቸው ለአፍሪካ ኩራት ነው  ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም