ቀጥታ፡

የፕሮፌሰር መስፍን ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ መስከረም  26/2013 ( ኢዜአ) የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስርዓተ ቀብር በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ዛሬ ተፈጽሟል።

በሥርዓተ ቀብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ተገኝተዋል።


ፕሮፌሰር መስፍን ኢትዮጵያዊነትን በማቀንቀን፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና ሠብዓዊ መብቶች መከበር ባደረጉት ትግልም የራሳቸውን አሻራ አሳርፈዋል።

በአካዳሚክ እውቀታቸውም በድርቅና ረሃብ፣ በማህበራዊና ሌሎች መስኮች ጥናትና ምርምሮችን አድርገዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም በ90 ዓመታቸው አርፈዋል።

ሥርዓተ ቀብራቸውም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም