የለንደን ማራቶንን በድል ያጠናቀቁ አትሌቶች አቀባበል ተደረገላቸው

87

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26/2013(ኢዜአ) ፕላቲንየም ደረጃ በተሰጠው 40ኛው የለንደን ማራቶንን በድል ያጠናቀቁ አትሌቶች በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 1:45 ላይ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበሉ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ኮማንደር አትሌት ማርቆስ ገነቲ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንትና አቶ ቢልልኝ መቆያ የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ በስፍራው ተገኝተው የጀግና አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ለቡድኑ አባላት እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ኬክ የቆረሱ ሲሆን የሁሉንም አትሌቶች ትኬት ወደ ቢዝነስ ክላስ ከፍ በማድረግ ወደ ሃገራቸው መመለሳቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም