ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 31 የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን በካፍ አካዳሚ እንዲገቡ ማድረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 31 የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን በካፍ አካዳሚ እንዲገቡ ማድረጉን አስታወቀ።

የብሔራዊ ቡድኑ አምስት ተጫዎቾች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውንም ገልጿል፡፡

ካሜሩን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት ከሁለት ቀን በፊት ለብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች ጥሪ ያደረገው ፌዴሬሽኑ ጥሪ ከተደረገላቸው 36 ተጫዋቾች መካከል አምስቱ የኮቪድ19 ቫይረስ እንደተገኘባቸው አስታውቋል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው አምስቱም ተጫዋቾች ራሳቸውን አግልለው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ተጨዋቾች ስም ሚዲያዎች ከመግለጽ እንዲቆጠቡም ፌዴሬሽኑ አስጠንቅቋል፡፡

አዲሱ የብሔራዊ ቡዱኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በህዳር መጀመሪያ አካባቢ ከኒጀር ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚካሄደው የማጣሪያ ጨዋታ ከሁለት ቀናት በፊት 41 ተጫዋቾች መምረጣቸው ይተወሳል፡፡

ከቫይረሱ ነጻ ሆነው ካምፕ የገቡት 31ዱ የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ዛሬ መስከረም 25ቀን 2013 ዓ/ም ረፋድ ላይ ልምምድ እንደሚጀምሩ ፌዴሬሽኑ ገልጿል፡፡

ከከሮና ቫይረስ ነፃ ሆነው ልምምድ የጀመሩት የብሔራዊ ቡድኑ አባላትም ከ72 ሰዓታት በኋላ ዳግም ምርመራ እንደሚደረግላቸው ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም