ሰላም ሚኒስቴር የ10 አመት መሪ እቅድ ላይ እየተወያየ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ሰላም ሚኒስቴር የ10 አመት መሪ እቅድ ላይ እየተወያየ ነው
አዲስ አበባ, መስከረም 22/2013 (ኢዜአ) የሰላም ሚኒስቴር የ10 ዓመት መሪ እቅዱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና፣ የአርብቶ አደር፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች አቅርቦ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ ላይ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስትር፤ ወ/ሮ አልማዝ መሰለ፣ የግብርና አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ እንዲሁም አቶ አየለ ነገሬ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተወካይ ተገኝተዋል።
ውይይቱ በዋናነት ዘላቂ የኢትዮጵያ ሰላም ግንባታ፤ በህግ የበላይነትና ደህንነት፤ እንዲሁም በፌደራሊዝምና ተመጣጣኝ ልማት ትብብርና ግንኙነት ዙሪያ የመጪዎቹ አስር አመታት መሪ እቅድ ላይ ያጠነጠኑ መሆኑተጠቅሷል።
በተጨማሪም በሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና የሪፎርም ተግባራትን እንደተካተተ ተገልጾአል።