ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ግዢ ከ90 በመቶ በላይ መጠናቀቁን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ - ኢዜአ አማርኛ
ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ግዢ ከ90 በመቶ በላይ መጠናቀቁን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ግዢ ከ90 በመቶ በላይ ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ቦርዱ ለአገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን እያደረገ ያለውን ዝግጅት እና በተለያዩ መጋዘኖቹ ገዝቶ ያከማቻቸውን የተለያዩ የምርጫ ቁሳቁሶችን ለጋዜጠኞች አስጎብኝቷል።
እንደ ኢብኮ ዘገባ ቦርዱ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ምርጫዎች በተለየ ምርጫን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማካሄድ የሚያስችል የምርጫ ቁሳቁሶች ግዢ ማድረጉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ሲተገበር የነበረው የምርጫ ሂደት እና ቀጣይ ሊደረግ የታቀደው የምርጫ ሂደት ምን እንደሚመስል በማነፃፀርም ቀርቧል።
ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የሚስጥር ድምፅ መስጫ ሳጥን ቀድሞው ከነበረው በጨርቅ የተሰራ መሸፈኛ ለየት ባለ ሁኔታ የተዘጋጀ ሲሆን መራጮች በሚስጥር የመረጡበትን የሚከቱበት ለእይታ ግልፅ የሆነ የድምፅ መስጫ ኮሮጆ መዘጋጀቱንም ለመመልከት ተችሏል።