የ8100 A የገቢ ማሰባሰቢያ እጣ ወጣ

70

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21/2013 ( ኢዜአ) የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ8100 A የገቢ ማሰባሰቢያ ሎተሪ እጣ ዛሬ በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ ይፋ ሆነ።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ8100 A አጭር የጽሁፍ መልእክት 2ኛ ዙር የሎተሪ እጣ አወጣጥ ሥነ-ስርዓት በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ ተካሂዷል።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ህብረተሰቡ ግድቡን እንዲደግፍ በ8100 A አጭር የጽሁፍ መልዕክት ማዘጋጀቱ ይታወቃል።

የግድቡን የመጀመሪያ የውሃ ሙሌት አስመልክቶ በ8100 A ለተሳታፊዎች የተዘጋጀው የሎተሪ እጣ አሸናፊም ዛሬ ተለይቷል።

በዚህም መሰረት የአሸናፊው እጣ ቁጥር 14 89 08 078 ሆኖ ወጥቷል፤ የእድለኛው የሞባይል ቁጥር ደግሞ 0930****71 ሆኗል።

የአስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤቱ አባል ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን እንዳሉት፤ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በ8100 A የገቢ ማሰባሰቢያ ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።

ባለፉት ስድስት ወራት በ8100 A የገቢ ማሰባቢያ 20 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገልጿል።

ህብረተሰቡ ወደፊትም በ8100 A አጭር የጽሁፍ መልእክት በመላክ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ድጋፍ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም