ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በፕሮፌሰር መስፍን ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ  መስከረም 20/2013 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳም በፕሮፌሰሩ ሞት ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ 
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን “የሐሳብ ልዕልና ምልክት፤ የሰላማዊ ትግል አርአያ፣ ላመኑበት ነገር እስከ መጨረሻቸው ሞጋች፣ ላመኑበት እውነት ብቻ የሚቆሙ" በማለት ገልጸዋቸዋል።

በእረፍታቸውም "ኀዘን ተሰምቶኛል፤ ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እመኛለሁ“ ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሺመልስ አብዲሳ በፕሮፌሰር መስፍን ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡

አቶ ሺመልስ ፕሮፌሰር መስፍን "ትልቅ የእውቀት አባት፣ ቁርጠኛ፣ ሰላማዊ ታጋይ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ላመኑበት ጉዳይ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ወደኋላ የማይሉ የጽናት ተምሳሌትና የአዲሱ ትውልድ አርአያ" ብለዋል፡፡

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለአድናቂዎቻቸው፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም