ቀጥታ፡

ለኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አንድ ሺህ ታብሌት ስልኮች በሥጦታ ተበረከተለት

አዲስ አበባ መስከረም 18/2013 (ኢዜአ) – ለኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኮቪድ-19 ምላሽ እንዲውል 102‚500 ዶላር የሚያወጣ አንድ ሺህ ታብሌት ስልኮች በስጦታ ተበረከተለት።

ሥጦታውን ያበረከተው ዞስክላስ የተባለ ድርጅት ከ10 ባለሀብቶችና ካምፓኒዎች ጋር በመተባበር መሆኑን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።

በሥጦታ የተሰጡት ታብሌት ስልኮች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ትልቅ አስተዋጾኦ እንዳላቸው የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው ዓባይነህ ገልጸዋል።

አቶ አስቻለው አክለውም ድርጅቱ ላደረገው ድጋፍ ምሥጋናቸውን አቅርበው፤ በቀጣይም ድጋፋቸውና ትብብራቸው እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም