ቀጥታ፡

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ  መስከረም 18/2012 ( ኢዜአ) አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የኢትዮጵያ ወንዶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የአሰልጣኙን ሹመት በማስመልከት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከመስከረም 15 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም የሚያቆይ የሁለት ዓመት ውል ተፈራርመዋል።

በዚህም መሰረት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ 125 ሺህ ብር የተጣራ ወርሃዊ ደመወዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ይከፈላቸዋል ተብሏል።

አሰልጣኝ ውበቱ ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሥራቸውን በይፋ መጀመራቸውም በይፋ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም