ቀጥታ፡

የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው

 አዲስ አበባ  መስከረም 16/2013 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሃይማኖት አባቶችና ምዕመናን በተገኙበት በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ፣ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

የደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ሥነ-ስርዓቶች እየተከናወኑ ሲሆን ዝማሬና ዜማ እየቀረበ ነው።

የዘንድሮው የደመራ በዓል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከልን መሰረት ባደረገ መልኩ ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ሥነ-ስርዓቱ ሳይጓደል አምስት ሺህ ተሳታፊዎች በሚገኙበት እንደሚከበር መገለፁ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም