ህብረተሰቡ የመስቀል ደመራ በዓልን ሲያከብር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ዘዴዎችን እየተገበረ መሆን አለበት

66

መስከረም 14/2013(ኢዜአ) ህብረተሰቡ የመስቀል ደመራ በዓልን ሲያከብር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ዘዴዎችን እየተገበረ መሆን እንዳለበት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የአዲስ አበባ ከተማ ሀገረ-ስብከት  ገለጸ፡፡

በሀገረ-ስብከቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ  መልዓከ ህይወት አባ ወልደየሱስ ለኢዜአ እንደገለጹት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክኒያት  የመስቀል ደመራ በዓልን በአደባባይ ማክበር አስቸጋሪ ነው፡፡  

በመሆኑም ሁሉም የእምነቱ ተከታዮች  የዘንድሮውን የደመራ በዓል ሲያከብሩ በጤና ባለሙዎች የሚነገሩ ምክረ-ሃሳቦቸን ሳይዘናጉ በጥንቃቄ መተግበር እንዳለባቸው ምከራቸውን ሰጥተዋል፡፡

በበሽታው ምክንያት ወቅቱ እንደልብ ወጥተው የሚዝናኑበት አይደለም ያሉት መልዓከ ህይወት አባ ወልደየሱስ ማንኛውም ሰው ርቀቱን በመጠበቅ፣ የፊት ማስክ በማድረግ፣ና በአንድ አካባቢ በብዛት ባለመሰባሰብ በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

̎ማንናኛውም ሰው ወጥቶ ሲመለስ ቤቱ የሚጠብቀው ልጁ ነው፣ሚስቱ ናት ፣ አባቱ ነው ፣እናቱ ናት፣እህት ወንድሙ ነው ወይም ሌላ የቅርብ ዘመዱ ነው፣ስለዚህ በሽታውን ቢያመጣ እነዙህ ሁሉ ወገኞችን እንደሚጎዳ ማሰብ አለበት ብለዋል፡፡

የ2013 የመስቀል በዓል ቅዱስ ፓትራሪኩና ብጹዓን አበው ጳጳሳት በሰጡት መመሪያ መሰረት በመስቀል አደባባይ በውስን ሰዎች የሚከበር ይሆናል ብለዋል መልዓከ ህይወት አባ ወልደየሱስ፡፡

በዓሉ ከመስቀል አደባባይ በቀጥታ በመገናኛ ብዙሃን የሚሰራጭ በመሆኑ ምዕመኑ በየቤቱ ሆኖ መከታተል እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

የመስቀል በዓል በመስቀል አደባባይ በውስን ሰወች ይከበር እንጅ ሃይማኖታዊ  ስነስረአቱ ሙሉ ለሙሉ የሚካሄድ ይሆናልም ብለዋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ በዓሉን ለማክበር  ወደ መስቀል አደባባይ መምጣት እንደማይጠበቅበት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም