ምክር ቤቱ በኮቪድ-19 ላይ ትናንት ያሳለፈው ውሳኔ የሚመራበት የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ወደሥራ እንዲገባ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ አሳሰቡ

64

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13/2013 ( ኢዜአ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮቪድ-19ን በመከላከል ቀጣይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ ትናንት ያሳለፈው ውሳኔ የሚመራበት የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ወደሥራ እንዲገባ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ አሳሰቡ።

አፈ ጉባኤው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮቪድ-19ን በመከላከል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ትናንት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በእዚህም አገራዊ ምርጫ ማካሄድ፣ ትምህርት ቤቶችን መክፈት፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማካሄድ፣ የጤና ተቋማት አሰራርና ቅንጅታዊ ሥራዎችን በተመለከተ በተላለፉ ውሳኔዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመሆኑም ስብሰባዎች፣ ህዝባዊ በዓላት፣ ስፖርታዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን የሚደነግጉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተቋማት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር መተግበር እንዳለባቸው አፈ ጉባኤው አሳስበዋል ።

የጤና ሚኒስቴርም የወጡ መመሪያዎችና ድንጋጌዎች በትክክል መፈጸማቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም