ሚኒስቴሩ ተቋርጦ የቆየውን ትምህርት መጀመር በሚያስችለው ስትራቴጂ ላይ እየተወያየ ነው

50

አዲስ አበባ፣መስከረም 12/2013 (ኢዜአ) ትምህርት ሚኒስቴር ተቋርጦ የቆየውን ትምህርት ዳግም መጀመር በሚያስችለው ስትራቴጂ ላይ ውይይት እያካሄደ ነው።

በስትራቴጂው መሰረት ትምህርት በተቋረጠበት ጊዜ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ የነበሩ ተማሪዎችን መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት ለማስጀመር ታስቧል።

ተቋርጦ የቆየውን ትምህርት በተለይ በከተሞች ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም በሶስት ፈረቃ ለመጀመር ታሳቢ መደረጉም በስትራቴጂው ተመልክቷል።

የተማሪዎችን ጥግግት ለመቀነስ ፈረቃው በቀናት እንደሚሆን ተገልጿል።

ይህም ሆኖ ተማሪዎች የሚበዙ ከሆነ በቀን በሶስት ፈረቃ ሊሆን እንደሚችልም ተመልክቷል።

በአንድ ፈረቃ ከ200 በላይ ተማሪዎች እንዳይኖሩ ይደረጋልም ነው የተባለው።

ስትራቴጂው አምስት ዋና ዋና ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን በቅንጅት መስራት፣ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት እንዲሁም የውሃ አቅርቦትና የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ ማሟላት የመጀመሪያዎቹ ናቸው።

የቤተሰብ ድጋፍ እንዲኖር ማድረግና የትምህርት ፕሮግራሙን ማጠናከርም በስትራቴጂው ተካተዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው ስትራቴጂ ውይይት ላይ ከሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች የተውጣጡ የትምህርት ቢሮዎች የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም