ለፕሬዝዳንት ትራምፕ መርዛማ ኬሚካል የያዘ ደብዳቤ በመላክ የተጠረጠረች አንዲት ሴት በቁጥጥር ስር ዋለች

75

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11/2013 ( ኢዜአ) ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መርዛማ ኬሚካል የያዘ ደብዳቤ በመላክ የተጠረጠረች አንዲት ሴት በቁጥጥር ስር መዋሏ ተገለጸ።

እንደ ሲ ኤን ኤን ዘገባ ራይሲን የተሰኘ አደገኛ መርዛማ ኬሚካል የያዘ ደብዳቤ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የላከችው ሴት ከካናዳ ወደ አሜሪካ ለመግባት ስትሞክር ነው ድንበር ላይ በቁጥጥር የዋለችው።

ኬሚካሉ ከፍተኛ መርዛማነት ያለው መሆኑና ወደ ሰውነት ውስጥ ከገባ የደም ውስጥ መፍሰስ እና ማስመለስ የሚፈጥር ሲሆን፤ የጉበትና የኩላሊት ሙሉ ለሙሉ ስራ እንዲያቆሙና ሞት እንዲከሰት እንደሚያደርግ ተጠቅሷል።

ሴትዮዋ በቁጥጥር በዋለችበት ሰዓት መሳሪያ ይዛ እንደነበርም ተገልጿል።

በዋሽንግተን ዲሲ የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ህጎች ክስ ይመሰርታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወደ ኋይት ሃውስ የሚላኩ ደብዳቤዎች ምርምራ በሚካሄድበት ማዕከል ውሰጥ በደብዳቤ ውስጥ የሚገኘው ኬሚካል ራይሲን መሆኑን ለማረጋገጥ ሁለት ምርመራ የተካሄደ መሆኑንም ተመልክቷል።

ከካናዳ ወደ ቴክሳስ የመንግስት ተቋማት በግለሰቧ በተለያዩ አድራሻዎች ተልከዋል ተብለው የተጠረጠሩ መልዕክቶች ላይ ምርመራ እየተከናወነ እንደሆነም ተገልጿል።

Top of Form

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም