ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሡልጣን ሐንፍሬ ዓሊ ሚራህ ሞት የተሰማቸው ሀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሡልጣን ሐንፍሬ ዓሊ ሚራህ ሞት የተሰማቸው ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10/2013(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሡልጣን ሐንፍሬ ዓሊ ሚራህ ሞት የተሰማቸው ሀዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቀድሞ የአፋር ክልል ፕሬዚደንትና በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስ ሀገራቸውን ያገለገሉት ሡልጣን ሐንፍሬ አሊ ሚራህ ሞት በመስማቴ እጅግ አዝኛለሁ ብለዋል።
በመሆኑም ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
የአፋር መንፈሳዊ መሪ ባደረባቸው ህመም በአዲስ አበባ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ74 ዓመታቸው ትናንት ሌሊት ከዚህ ዓመት በሞት ተለይተዋል።
ሱልጣን ሀንፋሬ አሊሚራህ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ የአፋር ህዝብ ሱልጣን በመሆን አገልግለዋል።
የሱልጣን ሀንፋሬ ስርአተ ቀብር ነገ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም በአሰኢታ ከተማ ይፈጸማል ተብሏል፡፡