ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጎርፍ ለተጎዱ ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጎርፍ ለተጎዱ ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10/2013 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአፋር ክልል በጎርፈ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ሰመራ ከተማ ገቡ።
ምክትል ከንቲባዋ ሰመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሃንፈሬ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች አቀባባል አድርገውላቸዋል።
ምክትል ከንቲባዋ ሰመራ የገቡት በክልሉ በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 12 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ምግብ ድጋፍ ለማድረግ ነው።
በክልሉ በአይሳኢታና አፋምቦ ከተማ በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ የጎርፍ ተጎጂዎችን እንደሚጎበኙ ታውቋል ።