የዲቦራ ፋውንዴሽን የማሰልጠኛ ማዕከል ምርቃት ስነስርዓት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የዲቦራ ፋውንዴሽን የማሰልጠኛ ማዕከል ምርቃት ስነስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2013(ኢዜአ) የዲቦራ ፋውንዴሽን የማሰልጠኛ ማዕከል ምርቃት ስነስርዓት እየተካሄደ ነው።
ቦሌ አካባቢ የሚገኘው እና የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያላባቸው ሰዎችን ለመደገፍ የተቋቋመው ዲቦራ ፋውንዴሽን የማሰልጠኛ ማዕከል ምርቃት ስነስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በስነስርዓቱ ላይ የዲቦራ ፋውንዴሽን ምስራች የአቶ አባ ዱላ ገመዳ ሁለተኛ መፅሐፍ የሆነው “ዲቦራ የብርሃን ጉዞ “ የተሰኘው መፅሐፍ ምርቃትም ይካሄዳል፡፡
ከተቋቋመ ሁለት አመታትን ያስቆጠረው ዲቦራ ፋውንዴሽን በእነዚህ ጊዜያት በአዕምሮ እድገት ውስንነት ላይ ለሚሰራ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሁለት ተሽከርካሪዎችን መስጠቱ ታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ መሰል ችግር ላለባቸው ቤተሰቦች የምግብ ድጋፍ ማድረጉም ተጠቁሟል፡፡
ከመፅሃፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ሙሉ ለሙሉ ፋውንዴሽኑን ለከማጠናከር ይውላል ነው የተባለው፡፡
በስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የቀድሞ እና የአሁን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡