ቀጥታ፡

በአፋር ክልል ከ35 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዷል

 አዲስ አበባ  መስከረም 9/2013 (ኢዜአ) በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ35 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት እቅድ መያዙን የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የዘንድሮው በጀት ዓመት የክልሉ የመስኖ ልማት ማስጀመሪያ ማርሃ ግብር ውይይት በሰመራ ከተማ ተካሂዷል።

የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ነኢማ መሃመድ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በተያዘው በጀት ዓመት ከ35 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዷል።

የመስኖ ልማቱ በተለይ የስንዴ ምርትን በስፋት በማከናወን ከውጭ ይገባ የነበረውን ተመሳሳይ ምርት ለማስቀረት ዓላማ ያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለእቅዱ ስኬት የሁሉም አካላት ጥረት ወሳኝ በመሆኑ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ፈቶ አሲም የመስኖ ልማቱ በክለሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል።

እርሳቸው አንዳሉት በዱብቲ፣ አሳይታ፣ አፍምቦ፣ ገዋኔ፣ አሚባራ፣ አዋሽ ፈንታሌ፣ እና ሚሌ ወረዳዎች ይተገበራል።


በአፋር ክልል ብቻ ከ304 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማት የሚቻል መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም