ቀጥታ፡

በሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የኤርትራውን ፕሬዝዳንት ለመቀበል ዝግጅት ተጠናቋል---የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

ሀዋሳ ሐምሌ 7/2010 የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ይጎበኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኮሚኝኑ ኮሚሽነር ዶክተር በላቸው መኩሪያ ለኢዜአ እንደገለጹት ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ዛሬ በሀዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ አቀባበል ይደረጋል፡፡ በሀገሪቱ ከሚገኙ ትላልቅ የመሰረተ ልማት ተቋማት ውስጥ አንዱ የሆነውን የሀዋሳ ኢንዱስትሪን የስራ እንቅስቃሴ ለፕሬዝዳንቱ ለማስጎብኘት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ በፓርኩ ሁሉም ኩባንያዎች በስራ ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት ኮሚሽነሩ እንቅስቃሴውን ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ለማሳየት አስፈላጊው መሰናዶ አጠናቀው እየተጠባበቁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ስለ ፓርኩ አደረጃጀትና ግንባታ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ ገለጻ ይደረጋል፡፡ የከተማዋ ህዝብ ፕሬዳንቱንና አብሯቸው የሚመጡት ልኡካናቸውን ለመቀበል በፈረስ ጉግስ ፣ በባህላዊ ስነስርዓትና በሌሎችም ዝግጅቶች ለመቀበል በመውጣት እንግዶችን እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም