በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 30 ሚሊዮን አለፈ

38

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8/2013(ኢዜአ) በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 30 ሚሊዮን ማለፉን የአሜሪካው ጆንስ ሆብኪን ዩኒቨርስቲ አስታወቀ።

በአለፈው አመት በቻይና ውሃን ከተማ የተቀሰቀሰው ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19 ) እስካሁን ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ   የ 940 ሽህ ስዎችን ህይዎት ቀጥፏል።

ቫይረሱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ አሜሪካ፣ ህንድ እና ብራዚል ከሌሎች ሃገራት ጋር ሲነጻጸር ክፉኛ ጉዳት የደረሰባቸው  ሀገራት ተብለው የተለዩ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ በአውሮፓ ሀገራት እንደገና  እያገረሽ መምጣቱ ተገልጿል።

የበሰሜን ንፍቀ ክበብ ሀገራትም የክረምቱን መግባት ተከትሎ ቫይረሱ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰባቸው መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ኤስያዊቷ ሀገር እስራዔልም ከዛሬ ጀምራ ለሁለተኛ ዙር በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሏ ታውቋል።

በአፍሪካ የምርመራ ሂደቱ ከፍጥነት አኳያ ክፍተት ቢኖርበትም  እስካሁን በተደረገ ምርመራ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን መብለጡ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም