ናይጄሪያዊያን ዶክተሮች አለግባብ ታካሚዎች ወደ ጤና ተቋማት እያመላለሱ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ናይጄሪያዊያን ዶክተሮች አለግባብ ታካሚዎች ወደ ጤና ተቋማት እያመላለሱ ነው
አዲስ አበባ መስከረም 7/2013 (ኢዜአ) ናይጄሪያዊያን ዶክተሮች አለግባብ ታካሚዎች ወደ ጤና ተቋማት እያመላለሱ መሆኑን አንድ የምርመራ ዘገባ ይፋ አደረገ።
ኦል አፍሪካ ‘ፕሪሚየም ታይምስ’ ጠቅሶ እንደዘገበው በናይጄሪያ ታዋቂ ስም ያላቸው የጤና ምርመራ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት ከሀኪሞችና ከሆስፒታሎች ጋር በመሆን በቢሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ ሲዘርፉ መቆየታቸውን ያሳያል።
የፕሪሚየም ታይምስ ጋዜጠኛ ለ20 ወራት ባደረገው ሚስጥራዊ የምርመራ ዘገባ የህክምና ባለሞያዎቹ ከሞያዊ ስነምግባር ውጭ የሆነ ተግር ሲከውኑ ቆይተዋል፡፡
ከህክማና ተቋማቱ አብዛኛዎቹ ለሚሰጡት አገልግሎት ላይ ህገወጥ በሆነ መንገድ ሞያዊ ስነምግባ በጣሰ መንገድ ከ10 እስከ 20 በመቶ የሚሆነውን ገንዘብ ለዶክተሩ እንዲከፈል አድርገዋል።
አንድ ማዕከልም ለምርመራ በተላከለት ሰው ቁጥር ዶክተሮች ለተለያዩ ክፍያዎች ሊጠቀሟቸው የሚችሏቸውን የስጦታ ካርድ እንዲሁም መኪናና ቤት ለመግዛት ብድር ለማግኘት የሚያስችላቸውን ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑም ተጠቅሷል።
ይህ በምርመራ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና በሀኪሞች መካከል የሚደረገው ሴራ በናይጄሪያ የህክምና አገልግሎት የሚሹ ሰዎች ላይ ጫና እያሳደረ እንደሆነ ተገልጿል።
የተቋሙ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኢድሪስ አኪንባጆ በምርመራ ዘገባው ውጤት መደናገጣቸውን መናገራቸውንና ፤ ይህ ታካሚዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳደረውና የአገሪቱ የጤና አገልግሎት ላይ አደጋ የሆነውን ሙስና ለማስቆም በፍጥነት የሚመለከታቸው አካላት ወደ እርምጃ ይገባሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ማለታቸውም ተመልክቷል።
የናይጄሪያ የሜዲካል ላብራቶሪ ተመራማሪዎች ማህበር ከጤና ተቋማት የሚላኩ ምርመራዎችን የሚያከናውን የትኛውም ማዕከል ከጤና ተቋማትና ከህክምና ባለሙያዎች ጋር ከ20 እስከ 40 በመቶ የሚደርስ ክፍያ እንደሚካፈል እርግጠኛ መሆን እንደሚቻል ጠቁሟል።
በመሆኑም ሀኪሞች የሚያገኙትን ጥቅም ለማሳደግ አላስፈላጊ ያልሆነ ተጨማሪ ምርመራ ሊያዙ ስለሚችሉ ይህም ታካሚዎችን ለተጨማሪ እንግልትና ወጪ ከመዳረጉም ባለፈ በፍጥነት መድሃኒት ካላገኙ እስከ ሞት የሚደርስ ጉዳት ሊያጋጥማቸው እንደሚችልም ተመልክቷል።