ቀጥታ፡

የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ለቆዳ አምራቾች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ መስከረም  7/2013 (ኢዜአ)የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) በኢትዮጵያ ለቆዳና የቆዳ ውጤት አምራቾች ድጋፍ አደረገ።

ኮይካ የኢትዮጵያ መንግስት የኮቪድ 19 ወረረሽኝን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ የ5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ከዚህ ውስጥ 500 ሺህ ዶላሩ  በወረርሽኙ ምክንያት ስራቸው የተቀዛቀዘባቸውን በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ የቆዳና የቆዳ ውጤት አምራቾችን ለመደገፍ ይውላል ተብሏል፡፡

ኮይካ ያደረገው ድጋፍ በጥቃንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው በኮሮና ወረረርሽኝ ስራቸው የተቀዛቀዘባቸው የቆዳና የቆዳ ውጤት አምራቾች የኮቪድ 19 መከላከያ ቁሳቁሶችን እንዲያመርቱ የሚያግዝ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ከመስከረም እስከ ታህሳስ 2013 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን ድርጅቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) በኢትዮጵያ የተለያዩ የልማት ፕሮግራሞችን ሲደግፍ መቆየቱ ይታወቃል።

ኢትዮጵያና ኮሪያ የቆየ ወዳጅነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም