አዲሱ የብር ኖት 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ታትሟል - ኢዜአ አማርኛ
አዲሱ የብር ኖት 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ታትሟል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4/2013(ኢዜአ) አዲሱ የብር ኖት 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ታትሞ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ለስርጭት ዘግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ አዲሱን የብር ኖት በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም አሁን ላይ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ታትሞ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የብር ኖት ቅያሬውን ለማከናወን ዝግጅቱ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
አዲሱን የብር ኖት ለማሳተም 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ውጭ መደረጉንም ተናግረዋል።
በሁሉም ክልሎች በበቂ ሁኔታ ለማድረስ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።
የብር ቅያሬው በውክልና የማይከናወን በመሆኑ መታወቂያ በመያዝ ባለቤቱ ብቻ ማከናወን ይኖርበታል ብለዋል።
ከአጎራባች አገራት የሚገባን ህገ ወጥ ገንዘብ ለመቆጣጠር በድንበር አካባቢ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግ መሆኑንም ዶክተር ይናገር ገልጸዋል።