ወረቀት አልባ የጉምሩክ አገልግሎት ተጀመረ

90

መስከረም 2/2012(ኢዜአ) ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታን ያስገኛል ተብሎ የሚጠበቀው ወረቀት አልባ የጉምሩክ አገልግሎት ዛሬ ማስጀመራቸውን ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ገለጹ።

አገልግሎቱ የኢኮኖሚ ሂደትን እንደሚያሳልጥና የንግድ ሥርዓት ዓለም አቀፍ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት እንዲጨምር የሚያበረታታ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በተገኙበት የተጀመረው የወረቀት አልባ ጉምሩክ አገልግሎት ምረቃ ስነ ሥርዓት ተከናውኗል።

አገልግሎቱ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት የንግድ ትስስር እንዲጠናከር፣ የጋራ የድንበር አስተዳደር ስርዓት በውጤታማነት እንዲከናወን፣ እንዲሁም በጉምሩክ እና በንግዱ ማህበረሰብ መካከል ጠንካራ ትብብር እንዲፈጠር ያስችላል ተብሏል።

የመረጃ አስተዳደርና ልውውጥ ስርዓትን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማዘመን፤ በጉምሩክ ስርዓት ሂደት ተጠያቂነት እና ግልጸኝነትን በመፍጠር፣ የሰነድ ማጭበርበርን በማስቀረት ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓት እንዲሰፍን አስተዋጽዖ እንደሚያደርግም መገለጹን ከጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ይህን የመሰሉ ዝመናዎች በየዘርፉ ተጠናሮ ይቀጥላል በማለትም ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ በፌስቡክ ገፀጻቸው አስፍረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም