ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5/2012 (ኢዜአ)  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ባስተላለፉት መልእክት ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

ከትናንት ትምህርት የምንቀስምበት፤ ዛሬን በጽናት የምንሰራበት፤ ነገን በተለወጠ አስተሳሰብ የምንኖርበት ዘመን ይሁንልን ብለዋል።

በአዲሱ ዓመት ለሁላችንም የምትሆን የበለፀገች ኢትዮጵያን የምትገነባበት ሰናይ ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም