የጉራጌ ወጣቶች ማህበር ዘርማ/አርዴ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 100 ሺህ ብር በስጦታ አበረከተ - ኢዜአ አማርኛ
የጉራጌ ወጣቶች ማህበር ዘርማ/አርዴ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 100 ሺህ ብር በስጦታ አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5/2012 (ኢዜአ) የጉራጌ ወጣቶች ማህበር ዘርማ እና በውጭ የሚኖሩ የጉራጌ ተወላጆች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ100 ሺህ ብር ስጦታ አበረከተ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የማንነታችን መገለጫ በመሆኑ በሙያ፣ በገንዘብና በጉልበት አሻራችንን እናሳርፋለን ብለዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እንደ ዘርማ ሁሉ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የወጣት አደረጃጀቶች በግድቡ ላይ አሻራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ አቅርቧል።
"የጉራጌ ወጣቶች ማህበር ዘርማ በውጭ ከሚኖሩ ኤማንዳ የጉራጌው ትግለንዳ" የጉራጌ ተወላጆች ጋር በመተባበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ100 ሺህ ብር ስጦታ አበርክተዋል።
የዘርማ ወጣቶች ለኢዜአ እንዳሉት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያዊያን የማንነታችን መገለጫ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።
እኛ የምንኖረው ሃገር ስትኖር ነው የሚሉት ወጣቶቹ የሉዓላዊነት መገለጫችን የሆነውን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለመደገፍ ተስማምተናል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ አመከላከቶች ቢኖሩም እንኳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ግን ምንም አይነት ልዩነት ሊኖር አይገባም ብለዋል።
በኢትዮጵያ ለሚገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የእውቀት፣ ጉልበትና ገንዘብ አስተዋጽኦ በማድረግ ፕሮጀክቶች የጋራ ሃብቶቻችን መሆናቸውን እናሳያለን ብለዋል።
"ዓባይ ፕሮጀክት ብቻ አይደለም" የሚሉት የጉራጌ ወጣቶች ማህበር ዘርማ አባላት አጀንዳ ተቀባይ ከመሆን ወጥተን በግድባችን ላይ የጋራ አቋም ሊኖረን ይገባል ብለዋል።
ግብጽ በቀጥታ ጦር ከማዝመት ይልቅ እርስ በእርስ እንድንጋጭ በማድረግ ጦርነቱን ቤታችን ድረስ ለማምጣት እየጣረች በመሆኗ፤ ለሰላማችንና ለልማታችን ስኬት በጋራ መቆም አለብን ብለዋል።
የጉራጌ ዞን የህዳሴው ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ አብራር መውደድ የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 132 ሚለዮን 868 ሺህ ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የዞኑ ነዋሪዎች ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ የሚሆኑ 19 በሬዎችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ እንስሳትን አበርክተዋል።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የጉራጌ ወጣቶች ዘርማ ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ከግድቡ የውሃ ሙሌት በኋላ በህብረተሰቡ ዘንድ የበለጠ መነቃቃት ተፈጥሯል ብለዋል
በመሆኑም በ2013 በጀት ዓመት በዞኑ 16 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ እቅድ ይዘው እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኮሙንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሃይሉ አብርሃም እንደገለጹት በነሃሴ 2012 ዓ.ም ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ የሚውል ከፍተኛ ገንዘብ ተሰብስቧል።
በነሃሴ ወር ሪከረድ የሆነ ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በቦንድ ግዥ በስጦታና 8100 ተሰብስቧል ብለዋል።
የህዳሴው ግድብ ከገንዘብ በተጨማሪ የወጣቶች ሰላማዊና የተደራጀ አንድነት ተገቢ ነው ያሉት አቶ ሃይሉ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የወጣት አደረጃጀቶች የዘርማን አርዓያ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በ2013 በጀት ዓመት ለግድቡ ግንባታ በተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች ሁለት ቢሊዬን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱንም ገልጸዋል።