የሱዳን መንግስት 1 ሺ 400 እስረኞችን ፈታ

76
አዲስ አበባ ግንቦት 2/2010 የሱዳን መንግስት በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ 1ሺ 400 ኢትዮጵያዊያንን መፍታቱ ተገለጸ። የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፤ እስረኞቹ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ተፈተዋል። ይህ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሱዳን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በሱዳን የታሰሩ ኢትዮጵያዊያንን እንደሚፈቱ ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር  ቃል በገቡት መሰረት ነው። ዶክተር አብይ አህመድ በሱዳን ሚያዚያ 24 እና 25 ቀን 2010 ዓ.ም ይፋዊ ስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በተለያዩ ምክንያቶች በሱዳን በእስር ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያን እንዲፈቱ ለፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር ጥያቄ አቅርበዋል። ፕሬዝዳንት አልበሽርም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጥያቄ መሰረት ኢትዮጵያዊያኑን እንደሚፈቱ ቃል በገቡት መሰረትም ዛሬ 1 ሺ 400 እስረኞች መፈታታቸው ታውቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም