ቀጥታ፡

ድርጅቱ ''ገበታ ለሀገር '' ፕሮጀክት የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4/2012 ( ኢዜአ) የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ''ገበታ ለሀገር'' ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ነጻነት ለሜሳ የተቋሙ ቦርድ ባደረገው ስብሰባ ''ገበታ ለሀገር'' ፕሮጀክት ድጋፍ ለማድረግ  መወሰኑን አስታውቀዋል።

በዚህ መሰረትም  ድርጅቱ በአዲሱ ዓመት 15 ሚሊዮን ብር፤ ቀሪውን  ደግሞ በ2014 ለመስጠት ወስኗል ብለዋል።

''ገበታ ለሀገር'' ፕሮጀክት በአማራ፣በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች እንደሚተገበር ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም