ቀጥታ፡

ፕሮፌሰር በየነ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ተሾሙ

አዲስ አበባ ጳግሜ 4/2012 (ኢዜአ) ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ተሹመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾመዋል።

ፕሮፌሰር በየነ በ1983 ጀምሮ በሰላማዊ ትግል ሚናቸውን ሲጫወቱ ኖረዋል፡፡

ፕሮፌሰር በየነ  በተቃዋሚ የፖለቲካ አመራርነት ለረዥም ጊዜ የቆዩና  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ምሁር ናቸው፡፡

በአሁኑ ጊዜም የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው፡፡

ፕሮፌሰር በየነ በኢትዮጵያ ፓርላማ ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም