ዓባይ የጥበቃ አሠሪዎች ማኅበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የ172 ሺህ ብር ቦንድ ገዛ - ኢዜአ አማርኛ
ዓባይ የጥበቃ አሠሪዎች ማኅበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የ172 ሺህ ብር ቦንድ ገዛ
አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 3/2012 (ኢዜአ) ዓባይ የጥበቃ አሠሪዎች ማኅበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የ172 ሺህ ብር የቦንድ ግዥ ማከናወኑን ገለጸ።
ማኅበሩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው አባላቱን በማስተባበር የ172 ሺህ ብር የቦንድ ግዥ ፈጽሟል።
በዕለቱ የማኅበሩ አባላት በአዲስ አበባ ቦሌ አራብሳ አካባቢ ችግኝ የተከሉ ሲሆን 22 የሚሆኑ የማኅበሩ አባላትም ደማቸውን ለግሰዋል።
የተከሏቸውን ችግኞች የሚንከባከቡ አትክልተኞችን በመቅጠር ለማሠራት መዘጋጀታቸውንም ማኅበሩ በመግለጫው አመልክቷል።