የብአዴን ድርጅታዊ ኮንፍረንስ ተጠናቀቀ

65
ባህር ዳር ግንቦት 2/2010 የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ማምሻውን ተጠናቀቀ፡፡ ኮንፍረንሱ ድርጅቱ ያጋጠሙትን ችግሮች ከገመገመ በኋላ ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ነው የተጠናቀቀው ፡፡ ብአዴን ችግሮቹን በመፈተሸ የአማራን ህዝቦች ጥቅም ለማስጠበቅና ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ  እንደሚሰራ ገልጿል፡፡ የሰላምና መረጋጋት ባለቤት ህዝቡ በመሆኑ ድርጅቱ በዚሁ ዙሪያ ህዝቡን በማሳተፍ ጠንክሮ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡ ከሚያዚያ 27 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2010 ድርጅታዊ ኮንፍረንሱ የተካሄደ ሲሆን፤ ''የተሃድሶ ንቅናቄያችን የበለጠ በማጥለቅ በማስፋትና ቀጣይነቱን በማረጋገጥ የህዝባችን የለውጥ ተስፋ እናስቀጥል'' በሚል መሪ ሃሳብ  ነው፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም